ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በመመከት አሜሪካ እና ቻይና ሲነጻጸሩ
በአሜሪካ የመጀመሪያዎቹ 15 ታማሚዎች በየካቲት 7 ሲገኙ ቻይና ውስጥ 68 ሺህ 500 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ነበር።
ከሁለት ሳምንት በኋላም በየካቲት 23 በቻይና የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከ80 ሺህን ሲበልጥ አሜሪካ ውስጥ ግን የቫይረሱ ታማሚዎች ከ100 በታች ነበር። በየካቲት 21 አሜሪካ ውስጥ የመጀመሪያው ሞት ሲመዘገብ ቻይና 2 ሺህ 943 ሞት አስመዝግባ ነበር። አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግን ነገሩ ተለዋውጧል። አሁን አሜሪካ የቻይናን 10 እጥፍ ሞት ያስመዘገበች ሲሆን አጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ዜጎቿ ቁጥርም ከቻይና ጋር ሲነጻጸር በተመሳሳይ በ10 እጥፍ ይልቃል።