ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ ሕይወት እንደገና በድንበር ላይ
ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ ሕይወት እንደገና በድንበር ላይ
ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሃያ ዓመታት ድንበሮቻቸውን ዘግተው፤ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ቆይተው ነበር። ጉዞ ተከልክሎ፣ ንግድና የስልክ ግንኙነት ተቋርጦ ነበር፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ቤተሰቦች ተቆራርጠው ቆይተዋል።
ሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ግን መስከረም 2011 ዓ.ም ድንበሩ ተከፈተ፤ ይህም በሁለቱም ወገን ያሉት ቤተሰቦች እንዲገናኙና ህይወታቸውን እንደገና እንዲጀምሩ እድል ሰጠ።
የዛላምበሳ ድንበር ዳግም ሲከፈት፤ ንግድ፣ ግንባታ፣ የቤተሰቦች ህይወት እንደ አዲስ አንሰራራ።
ነገር ግን ድንበሩ ዳግመኛ ለንግድና ለተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተዘጋ። በእርግጥ የድንበር እንቅስቃሴው በእግርና መደበኛ ባልሆነ መልኩ ቀጥሏል።
በድንበሩ አካቢ ያሉ ሕዝቦች ነገን በተስፋ አሻግሮ ይመለከታሉ፤ ነገር ግን የሰዎችና የንግድ እንቅስቃሴው መቀዛቀዝ ተስፋ መቁረጥንም እየጋበዘ ነው።
በዚህ ዘጋቢ ፊልም የአንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ቤተሰብን እና በሁለቱም ወገን የሚኖሩ ዘመዶቹን ሕይወት እንከተላለን። የመጀመሪያ ልጃቸውን ክርስትና ሲያስነሱ አብረናቸው እንሆናለን፤ ስለሥራቸውና ስለመጻዒ ህይወታቸው ያላቸውን ተስፋ እንሰማለን።
እድሜውም ሙሉ ፎቶግራፍ ሲያነሳ የኖረ ግለሰብም አብሯቸው አለ፤ በዛላምበሳ ከተማ ለሁለቱም ሕዝቦች መገናኛ ይሆናል በሚል ተስፋ ሆቴል የሚገነባ ኤርትራዊ ነጋዴም አግኝተናል።