በኮሮናቫይረስ የተያዘች ሚስቱን ተንከባክቦ ያዳነው ባል ታሪክ

እነዚህ ጥንዶች የኮሮናቫይረስ በተከሰተባት ቻይና፤ ዉሃን ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። ሴቷ ነርስ ስትሆን ከወራት በፊት በታኅሳስ አጋማሽ መታመም ጀመረች። ያኔ ታዲያ የታመመችው ኮሮናቫይረስ ነበር። ባሏ ደግሞ የፊልም ሞያተኛ ነው። የየዕለት ተግባራቸውን ይቀርጻል። ባለቤቱ በታመመችበት ወቅትም አጠቃላይ ሂደቱን ቀርጾ በሚከተለው መልኩ ለዓለም አጋርቷል።