ወረርሽኝ ምንድን ነው? እስካሁን በዓለም የተከሰቱት ወረርሽኞችስ ምን ዓይነት ነበሩ?
ዓለማችን በተለያዩ ጊዜያት መጠናቸውና ዓይነታቸው የተለያዩ ወረርሽኞችን አስተናግዳለች። ለመሆኑ ወረርሽኝ ምንድን ነው? የሜሪያም ዌብስተር መዝገበ ቃላት እንደዚህ ይተረጉመዋል። "ወረርሽኝ ማለት አንድ በሽታ በሰፊ ቦታ ላይ ሲከሰትና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ሲይዝ ነው።"
በተለያዩ ጊዜያት በኣለም ዙሪያ የተከሰቱት ወረርሽኞች በርካታ ቁጥር ያለው ሰው ያጠቁ ሲሆን በፈረንጆቹ በ1918 አካባቢ የተከሰተው ስፓኒሽ ፍሉ ግን በገዳይነቱ ተወዳዳሪ የለውም። በወቅቱ በዚሁ ወረርሽኝ ሳቢያ 50 ሚሊዮን ሕዝብ መሞቱ ይነገራል።