የጥቁር አንበሳ አርበኞች ድል

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የጥቁር አንበሳ አርበኞች የጣሊያንን አውሮፕላኖችን አስወርደው ድል ተቀዳጅተዋል።

ለታሪክ የተቀመጡትና በጥቁር አንበሳ አርበኞች ድባቅ ተመተው የወረዱት የጣሊያን አውሮፕላኖች ቅሪት እስካሁን አለ።

የድሮ ቀለማቸው ወይም ሙሉ ቅርፃቸው ለቆና እንዳልነበሩ ቢሆኑም የድሉ ምልክት መሆናቸውን እንደቀጠሉ ነው።

በተለይ በምሥራቅ ወለጋ ላሉት የቦኒያ ሞሎ ነዋሪዎች ልዩ ትርጉም አለው።