የደመራ በዓል አከባበር ምን ይመስል ነበር?

አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የነበረውን ደመራ አከባበር ምን እንደሚመስል የሚያሳዩ ምስሎችን አቅርበንላችኋል።

በአዲስ አበባ የተከበረው የደመራ በዓል
የምስሉ መግለጫ, የደመራ በዓል በመላ ሃገሪቱ በድምቀት ተከብሯል።
የደመራ አከባበር በአዲስ አበባ
የምስሉ መግለጫ, መስቀል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች ዘርፍ የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል።
በአዲስ አበባ ነበረው መስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, በዓሉ እ.አ.አ በ2013 ነበር በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, ዩኔስኮ መስቀልን በዓለም ቅርስነት የመዘገበው አዘርባይጃን በተካሄደው 8ኛው የማይዳሰሱ ቅርሶች ኮንፈረንስ ላይ ነበር።
የመስቀል በኣል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የመስቀል በዓል በየዓመቱ መስከረም 17 ይከበራል።
የመስቀል በዓል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የደመራ በዓል ደግሞ መስከረም 16 ይከበራል።
የመስቀል በዓል አከባበር በአዲስ አበባ
የምስሉ መግለጫ, በበዓሉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሳታፊ ይሆናሉ።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የ2010 የደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እንዲህ ደምቆ ተከብሯል።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የመስቀል በዓል ከሐይማኖታዊነቱ በተጨማሪ ባህላዊ እና ማሕበራዊ ዕሴቶች አሉት።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ቅዱስ ባስልዮስ ማር ቶማ ጳውሎስ ሁለተኛ በዘንድሮው በዓል ላይ ተገኝተዋል።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የመስቀል በዓል የክረምቱን መውጣት የሚያመላክት ተደርጎም ይቆጠራል።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, በዓሉ የቱሪስት መስህብ በመሆንም ያገለግላል።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የደመራ በዓል ወዳጅ ዘመድ አንድ ላይ የሚያከብረው ልዩ በዓል ነው።
የመስቀል አከባበር
የምስሉ መግለጫ, የመስቀል አከባበር በአዲስ አበባ