እስራኤል በጋዛ ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ አጠንክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

የፎቶው ባለመብት, Israeli Defence Forces (IDF
የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት የአገራቸው ሠራዊት በጦርነቱ የሚያካሂደው ዘመቻ ያለበት ደረጃ “መቀየሩን” በመግለጽ፣ “ተጨማሪ መረጃ አስኪሰጥ ድረስ” ዘመቻው ይቀጥላል ብለዋል።
አርብ ምሽት ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ “የጋዛ ምድር ተንቀጥቅጣለች” በማለት የመከላከያ ሚኒስትሩ ለአንድ ቴሌዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
“ከመሬት ላይ እና በአየር ጥቃት ፈጽመናል። በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ሽብርተኞች ላይ በያሉበት ጥቃት ፈጽመናል።
ለሠራዊታችን የተሰጠው መመሪያ ግልጽ ነው፡ ተጨማሪ መግለጫ አስከሚሰጥ ድረስ ዘመቻው ይቀጥላል” ብለዋል።
ከአርብ ምሽት ጀምሮ በተጠናከረ ሁኔታ የእስራኤል ጦር ኃይል በጋዛ ላይ የሚያካሂደው ጥቃት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ወደ ተወሰኑ የጋዛ ክፍሎች የእስራኤል ወታደሮች ዘልቀው መግባታቸው ተነግሯል።




















