ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ የኑክሊየር ኃይል በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዙ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአገራቸው ሠራዊት የኑክሌር ኃይል ‘በተለየ ሁኔታ በተጠንቀቅ’ እንዲቆም አዘዙ። ፕሬዝዳንት ፑቲን የአገራቸውን መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሹይጉን ጨምሮ ለከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ “ተገቢ ያልሆነ” እርምጃ እና “ሕገ ወጥ ማዕቀብ” መጣላቸውን ተናግረዋል።
የቀጥታ ሽፋን
አዲሱ የገንዘብ ዝውውር ማዕቀብ ሩሲያን ምን ያህል ይጎዳታል?
ፑቲን የኒውክሌር ቁልፉን ይጫኑት ይሆን?
በዩክሬን ጦርነት ሳቢያ በፕሬዝዳንት ራማፎሳና በሚኒስትራቸው መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ተዘገበ
በጦርነት ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከዩክሬን መሸሻቸው ተነገረ
አንድ ሺህ የሚሆኑ ዩክሬናዊያን ጎብኚዎች ከዛንዚባር መሄጃ አጥተዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የሩሲያ ወረራ ተከትሎ የዩክሬን የአየር ክልል ለሲቪል በረራዎች በመዘጋቱን 1,000 የሚሆኑ የዩክሬን ቱሪስቶች በታንዛኒያዋ ራስ ገዝ በሆነችው የዛንዚባር ደሴቶች መሄጃ አጥተው ተቀምጠዋል።
የዛንዚባር ባለስልጣናት ጎብኚዎቹን ወደ ፖላንድ ለማጓጓዝ በጎረቤት አገር ኬንያ ከሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ገልጿል።
የቱሪዝም ሚኒስትሯ ለይላ መሐመድ ሙሳ የቱሪስቶች ደህንነት እና ጤንነትን እየተከታተልኩ ነው ብለዋል።
ቱሪስቶቹ ያረፉባቸው አንዳንድ ሆቴሎች የዋጋ ቅናሽ ያደረጉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ለረዥም ጊዜ ለቆዩ እንግዶች በነጻ መስተንግዶ እየሰጡ ነው።
የዛንዚባር የባህር ዳርቻ እና ታሪካዊ ባህሉ የውጭ ቱሪስቶች ትልቅ መስህብ ነው።
ከቱሪስቶቹ አንዱ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በሆቴሎቻቸው ሆነው የዩክሬን ሁኔታ እየተከታተሉ ነው።
በተገኘው አጋጣሚ ወደ ሃገራቸው ወደሚቀርብ ቦታ እንደሚገወጓዙ ተስፋ አላቸው።
ፕሬዝዳንት ፑቲን የሩሲያ የኑክሊየር ኃይል በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዙ

የፎቶው ባለመብት, EPA
የምስሉ መግለጫ, ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የአገራቸው ሠራዊት የኑክሌር ኃይል ‘በተለየ ሁኔታ በተጠንቀቅ’ እንዲቆም አዘዙ።
ይህም ለሩሲያ ኑክሌር ተሸካሚ ስልታዊ የሚሳኤል ኃይል የተሰጠ ከፍተኛው የተጠንቀቅ ትዕዛዝ ነው።
ፕሬዝዳንት ፑቲን የአገራቸውን መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሹይጉን ጨምሮ ለከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ “ተገቢ ያልሆነ” እርምጃ እና “ሕገ ወጥ ማዕቀብ” መጣላቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ትዕዛዝ ያስተላለፉት የኔቶ አባል አገራት በሩሲያ ላይ “ጠብ አጫሪ መግለጫዎችን” እያወጡ ነው በማለት ሞስኮ ከከሰሰች በኋላ ነው።
ፑቲን አገራቸው የኑክሊየር ጦር መሳሪያን ልትጠቀም እንደምትችል በተዘዋዋሪ ሲናገሩ የቆየ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ባደረጉት ንግግር ደግሞ “ማንም ሊያስቆመን ቢሞክር የሚሰጠው ምላሽ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ይሆናል” ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።
አሁን ፕሬዝዳንቱ ለአገራቸው ጦር ሠራዊት የኑክሌር ኃይል ያስተላለፉት የተጠንቀቅ ትዕዛዝ አስገዳጅ ሁኔታ ቢከሰት በፍጥነት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ቢሆንም ግን አሁን ባለው ሁኔታ በሩሲያ በኩል የኑክሌር ጦር መሳሪያን ለመጠቀም ፍላጎት አለ ማለት እንዳልሆነ እየተነገረ ነው።
ሩሲያ በዓለም ላይ ካሉ አገራት ሁሉ ከፍተኛ መጠን ያለው የኑክሌር አረር ያላት ሲሆን፣ የኔቶ አባል አገራት በአንድ ላይ ሩሲያን ሊያወድም የሚችል የኑክሌር አቅም አላቸው።
አሁን ፑቲን ለሠራዊታቸው ያስተላለፉት ትዕዛዝ አላማ የኔቶ አባል አገራት ለዩክሬን የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ ፍርሃት ለመፍጠርና ሩሲያ ያላትን ኃይል የት ድረስ ልትጠቀም እንደምትችል ለማሳየት እንደሆነ ተንታኞች እየገለጹ ነው።
የዩክሬን ጦር ካርኪቭን መልሶ ተቆጣጠረ

የፎቶው ባለመብት, BlackSky
የዩክሬን ጦር ቁልፍ የምትባለውን የካርኪቭ ከተማን መልሶ መቆጣጠሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።
ኦሌህ ሲንዬሁቦቭ በቴሌግራም ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ “ካርኪቭን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረነዋል" ብለዋል።
አክለውም "የታጠቁ ሃይሎች፣ፖሊስ እና መከላከያ ሰራዊት በጋራ እየሰሩ ሲሆን ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ከጠላት እየጸዳች ነው።" ብለዋል
የሩስያ ወታደሮች በአንድ ጀምበር የዩክሬን ሁለተኛ ትልቅ ወደሆነችው ከተማ መግባት ችለው ነበር።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ቪዲዮዎች በዩክሬን እና በሩሲያ ወታደሮች መካከል የጎዳና ላይ ጦርነት እንደነበር አሳይቷል።
መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ተለዋዋጭ ሲሆን የትኛው አካል የትኛውን ግዛት ተቆጣጥሯል የሚለውንም ለማጣራት አስቸጋሪ ሆኗል።
ነገር ግን መሬት ላይ ያሉ የአይን እማኞች ካርኪቭ በዩክሬን ቁጥጥር ስር መሆኗን እና በጎዳናዎች ላይ ያለው ግጭት እየቀለለ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በዩክሬኗ መዲና ኪዬቭ ምን አዲስ ነገር አለ?

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የሩስያ ወታደሮች የዩክሬን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ ወደሆነችው ካርኪቭ የገቡ ሲሆን በዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ ዙሪያም ዛሬም ጥቃቶች ቀጥለዋል።
የሩስያ ሚሳኤል ትናንት ሌሊት በከተማይቱ አቅራቢያ ጥቃት ካደረሰ በኋላ በኢንተርኔት ላይ የተጋሩ ምስሎች የእሳት ነበልባል እና ጭስ አሳይተዋል ።
አንደኛው ጥቃት የተፈጸመው ከዋና ከተማዋ በስተደቡብ ምዕራብ በምትገኘው ቫሲልኪቭ ከተማ የሚገኝ የነዳጅ ማጠራቂሚያ ላይ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ እሳትም አስነስቷል።
የከተማው ከንቲባ ናታሊያ ባላሲኖቪች "ጠላት ሁሉንም ነገር ማጥፋት ይፈልጋል" ብለዋል።
የሩሲያ ጦር ከተማዋን በከበባት በአሁኑ ወቅት የኪዬቭ ባለስልጣናት ዜጎቻቸው ቤት ውስጥ እስከ ሰኞ ጥዋት ድረስ እንዲቆዩ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ይህንን ትዕዛዝ ተላልፈው በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ “የጠላት ተላላኪ ቡድኖች አባል እንደሆኑ ይቆጠራሉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቦምብ መጠለያዎች እና በባቡር ጣቢያዎች ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ከተማዋን ለመከላከል በባለሥልጣናት የተከፋፈሉ ጠመንጃዎችን በመውሰድ እየታገሉ ይገኛሉ።
ከ 200 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል- የዩክሬን ባለስልጣን

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የዩክሬን መንግሥት እንባ ጠባቂ ሉድሚላ ዴኒሶቫ እንደተናገሩት በሩሲያ ወረራ ከ210 በላይ የዩክሬን ሲቪሎች ሲገደሉ ከ1 ሺህ 100 በላይ ቆስለዋል።
"በማይታይ ጭካኔ ጠላት የመኖሪያ ሕንፃዎችን፣ ሆስፒታሎችን፣ መዋእለ ሕጻናት እና ትምህርት ቤቶችን እያወደመ ነው። ከዩክሬን ምድር ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ህጻናትን ጨምሮ የመኖር መብትን እየነጠቀ ነው" ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ገልጸዋል።
ዴኒሶቫ በኪዬቭ በሚገኝ ሆስፒታል በተተኮሰ ጥይት የተገደለ ሕፃን እና በካርኪቭ በሚሳኤል የመኖሪያ ሕንፃ መመታቱን ተከትሎ የተገደለችውን ሕፃን ጨምሮ የአንዳንድ የሲቪል ሰዎች ሞት ምሳሌዎችን ሰጥታዋል።
ሩሲያ "ለእነዚህ ወንጀሎች ከባድ ቅጣት እንድትቀጣ" ጠይቃዋል።
“ዩክሬን እነዚህን ሁሉ ሁነቴዎች እየመዘገበች ነው። እናም በሄግ ለጦር ወንጀል ፍርድ ቤት ታስተላልፋለች” ሲሉ ተናግረዋል።
ዩክሬን 4 ሺህ 300 ሩሲያውያን መሞታቸውን አስታወቀች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የዩክሬን ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር የዩክሬን ጦር እስካሁን በሩሲያ ላይ ያደረሰውን ኪሳራ ግምት ይፋ ያደረጉ ሲሆን በዚህም 4 ሺህ 300 ሩሲያውያን ሞተዋል ብለዋል።
የኪዬቯ ሃማ ማሊያ በግጭቱ የመጀመሪያዎቹ ሶስት ቀናት ውስጥ ደረሱ ያሏቸውንና በመጪው ቀናቶች ሊቀየሩ የሚችሉ ከሩሲያ በኩል የደረሱትን ኪሳራዎች በፌስቡክ ገጻቸው አጋርተዋል ።
የሩስያ ወታደራዊ ኪሳራዎች ተብለው ከዩክሬን በኩል የተገለጹት
- 4,300 ሩሲያውያን ሞተዋል
- 27 አውሮፕላኖች ወድመዋል
- 26 ሄሊኮፕተሮች
- 146 ታንኮች
- 706 የታጠቁ የጦር መኪኖች
- 49 መድፍ
- 1 የአየር መከላከያ
- 4 በርካታ የሮኬት ማስጀመሪያዎች
- 30 ተሽከርካሪዎች
- 60 ታንከሮች
- 2 ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች)
- 2 ጀልባዎች መውደማቸውን አስታውቀዋል
በርካታ አገራት ድጋፋቸውን ለዩክሬን እየላኩ ነው

የፎቶው ባለመብት, EPA
ግሪክ ለዩክሬን "የመከላከያ መሳሪያዎችን" እና የሰብአዊ እርዳታን እንደምትልክ ተናግራለች።
የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንደዘገበው ሁለት ወታደራዊ ማመላለሻ አውሮፕላኖች እሁድ ወደ ጎረቤት ፖላንድ እንደሚያመሩ ገልጿል።
ነገር ግን አውሮፕላኖቹ የሚይዙት መሳሪያ ዝርዝር መረጃ አልተገለጸም።
የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ መንግስታቸው 1 ሺህ ጸረ ታንክ እና 500 የየሚሳኤሎች መቃወሚያ ወደ ዩክሬን እንደሚልኩ አስታውቀዋል።
ብሪታንያም ለዩክሬን የጦር መሳሪያ አቅርቦትን ለመደገፍ ቃል ከገቡ ከ25 በላይ ሀገራት አንዷ ነች።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ "ዩክሬንን የሚደግፍ ጠንካራ ጥምረት" ምስረታን በደስታ ተቀብለዋል ።
"ድጋፉ እየደረሰን ነው። መሳሪያ፣ መድሃኒት፣ ምግብ፣ ናፍጣ እና ገንዘብ እየተቀበልን ነው" ሲል አክለዋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ለሩሲያ ልዩ ሃይሎች ምስጋናቸውን ገለጹ

የፎቶው ባለመብት, Anadolu Agency via Getty Images
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን "ወታደራዊ ግዴታቸውን በጀግንነት ተወጥተዋል ያሏቸውን የሀገሪቱን ልዩ ሃይሎች አመስግነዋል።
በክሬምሊን ድረ-ገጽ ላይ በታተመው የቴሌቭዥን መግለጫቸው ላይ ፑቲን "በሩሲያ ህዝብ እና በታላቋ እናት ሀገራችን ስም" በሚል ምስጋናቸውን አቅርበው፣ እያደረጉት ላለው "እንከን የለሽ አገልግሎታቸው" አድናቆታቸውን ችረዋል።
ፑቱን ከሩሲያ ወረራ በፊት በራስ ገዝነት አገራት ዕውቅና የሰጧቸውን በምስራቃዊ ዩክሬን ውስጥ በአማፅያን የተያዙ ሁለት አካባቢዎችን በመጥቀስ፣ ወታደሮቹ ለዶንባስ የህዝብ ሪፐብሪክ እርዳታ እንዲሰጡ ትዕዛዝ ተላልፎላቸው ነበር ብለዋል።
"የልዩ ኦፕሬሽን ሃይሎችን ሰራተኞች፣ የልዩ ሃይል ክፍል አዛዦች፣ በአጠቃላይ ጦሩ ለቃላችሁ ባሳያችሁት ታማኝነት በሩሲያ ህዝብ እና በታላቋ እናት ሀገራችን ስም ለሰጣችሁት እንከን የለሽ አገልግሎታችሁ ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ" ብለዋል
አክለውም “መልካም እድል፣ ስኬት እና መልካሙን ሁሉ ለእናንተ እና ለምትወዷቸው ሰዎች እመኛለሁ” በማለት መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከአለም አቀፉ ጁዶ ፌዴሬሽን ታገዱ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
አለም አቀፉ የጁዶ ፌዴሬሽን ቭላድሚር ፑቲንን ከፌዴሬሽኑ ክብር ፕሬዝዳንትነት እና አምባሳደርነት አግዷቸዋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን የጁዶ ጥቁር ቀበቶ አላቸው።
ውሳኔው በቅርብ ቀናት ውስጥ ከታወጁ በርካታ የስፖርት “ማዕቀቦች” አንዱ ነው።
በመስከረም ወር በሶቺ ሊካሄድ የነበረው የሩስያ ፎርሙላ 1 ግራንድ ፕሪክስ የመኪና ውድድር ተሰርዟል።
እንዲሁም በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ የ2022 የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ከሴንት ፒተርስበርግ ይልቅ በፓሪስ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ሩሲያ በተመድ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷ እንዲገፈፍ ዩክሬን ጠየቀች

የፎቶው ባለመብት, AFP
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ሩሲያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷ እንዲገፈፍ እየጠየቁ ነው - ሩሲያ በዩክሬን የፈፀመችው የወንጀል ድርጊት "የዘር ማጥፋት" ላይ ደርሷል ብለዋል።
የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት፣ ሩሲያ በአውሮፓውያኑ 1945 ጀምሮ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል ከሆኑ አምስት ሀገራት አንዷ ነች። ይህም ምክር ቤቱ በሚያደርጋቸው ማንኛውም “ተጨባጭ” ውሳኔዎች ላይ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ይሰጣታል።
በያዝነው ሳምንት አርብ እለት የፀጥታው ምክር ቤት የሩሲያን ጥቃት በማውገዝ እና ጦሯን ከዩክሬን እንድትወጣ የሚጠይቀውን የውሳኔ ሃሳብ ለማገድ ሩሲያን ድምፅ በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማለች።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጦርነቶችን ለማስወገድ እና ሰላምን ለማስፈን የተቋቋመው ምክር ቤት ሌሎች አራት ቋሚ አባላት ያሉት ሲሆን እነሱም አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ቻይና ናቸው።
ቢያንስ 200 ሺህ የሚሆኑ ዩክሬናውያን ወደ ሶስት ጎረቤት ሃገራት ተሰደዋል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ለአራት ቀናት የቀጠለው ጦርነት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን ወደ ጎረቤት ሃገራት እየተሰደዱ ነው።
የስሎቫክ ባለስልጣናት ቅዳሜ እለት እንዳሳወቁት በባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ዩክሬናውያን በሶስት ድንበሮች በኩል ወደ አገሪቱ ተሻግረዋል።
ይህ ከመደበኛው አኃዝ አሥር እጥፍ ያህል ነው።
ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ባሉት ሶስት ቀናት ውስጥ ከ43 ሺህ በላይ ዩክሬናውያን ወደ ሮማኒያ የተሰደዱ ሲሆን ከ150 ሺህ በላይ ሰዎች ፖላንድ ገብተዋል።
ዩክሬን ሌሎች አራት አገሮችን ትዋሰናለች ከነዚህም መካከል ሃንጋሪ እና ሞልዶቫ በሺዎች የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን ተሻግረው የገቡባበቸው አገራት ናቸው።
የዩክሬን ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ይሆን?
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት በቤላሩስ ከሩሲያ ጋር እንደማይነጋገሩ ገለጹ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሩሲያ የልዑካን ቡድኗ ከዩክሬን ጋር ለመነጋገር በሚመስል መልኩ ቤላሩስ መድረሱን ተናግራለች
ነገር ግን የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ሩሲያ ዩክሬንን ከቤላሩስ ግዛት ባታጠቃ ኖሮ በቤላሩስ ዋና ከተማ ሚንስክ ላይ ድርድር ማድረግ ይቻል ነበር ሲሉ የቀረበላቸውን ጥሪ ውድቅ አድርገውታል።
ሆኖም በሌሎች ስፍራዎች ላይ ድርድር እንዲካሄድ በሩን ክፍት አድርገውታል።
“ከግዛታችሁ ጥቃት ባይሰነዘር ኖሮ፣ በሚንስክ ልንነጋገር እንችል ነበር...ሌሎች ከተሞች የውይይት መድረኮች ሊሆኑ ይችላሉ።" ብለዋል።
"በእርግጥ እኛ ሰላም እንፈልጋለን፤ መገናኘት እንፈልጋለን፤ ጦርነቱ እንዲያበቃ እንፈልጋለን። ዋርሶ፣ ብራቲስላቫ, ቡዳፔስት፣ ኢስታንቡል፣ ባኩ የመሳሰሉ ከተማዎች ከሩሲያ ጋር ለመገናኘት በአማራጭነት አቅርበንላቸዋል" በማለት አስረድተዋል።
"ሌላ ማንኛውም ከተማ ይስማማናል ይህም ማለት ግዛታቸውን በኛ ላይ ለሚደርስ የሚሳይል ጥቃት ያልሰጡ። በዚህ መንገድ ብቻ ነው ድርድሩ ሐቀኛ መሆን የሚችለውና እና በእርግጥ ጦርነት ማቆም የሚቻለው" ብለዋል ፕሬዚዳንቱ
ሩሲያ ተጨማሪ ከተሞችን እንደዘጋች አስታወቀች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በዩክሬን የተለያዩ ከተሞች እና መሠረተ ልማት ላይ ተጨማሪ ጥቃቶች እንዳሉ ሪፖርቶች እየወጡ ይገኛሉ።
የሩስያ ሃይሎች ኬርሶን እና በርዲያንስክ የተባሉ ከተሞችን ዘግተው በዩክሬን ወታደራዊ መሠረተ ልማት ላይ ተጨማሪ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሳቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢጎር ኮናሼንኮቭ ተናግረዋል።
ዩክሬን በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ኬርሶንን መልሳ መያዟ ተሰምቷል።
ከተማዋ ከዩክሬን በስተደቡብ፣ ከክሬሚያ በሰሜን-ምዕራብ የምትገኝ ሲሆን በርዲያንስክ ከክሬሚያ በስተምስራቅ የምትገኝ የወደብ ከተማ ነች።
ኮናሼንኮቭ እንዳሉት የሄኒቼስክ ከተማ እና በኬርሶን አቅራቢያ የሚገኘው የቾርኖባይቭካ አየር መንገድም በቁጥጥር ስር ውለዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ የሩስያ ጦር በትናንትናው ዕለት የዩክሬንን ወታደራዊ መሠረተ ልማት በአየር እና በባህር ላይ በተወነጨፉ ክሩዝ ሚሳኤሎች ደብድቧል።
"አለም እንዲህ እንታገላለን ብሎ አላመነም" ዩክሬን

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ለአራተኛ ቀን በቀጠለው ጦርነት የዩክሬን ህዝብ በትግሉ ጸንቶ የቀጠለ ሲሆን የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ዓለም ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦሌክሲይ ሬዝኒኮቭ " በባለፉት 72 ሰዓታት በነበረው ትግል ህዝቡ የሩስያን ጥቃት መመከት እንደሚቻል ለአለም አረጋግጧል" ብለዋል።
በተያያዘ ዜና በዋና ከተማዋ ኪዬቭ ለዩክሬን በበጎ ፈቃደኝነት መሳተፍ ለሚፈልጉ የውጭ ዜጎች የጦር ክፍልም እያቋቋመ ነው።
"ይህ ለአገራችን የምትሰጡት ትብብር ማሳያ ይሆናል" በማለት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ አዲሱ ስለሚቋቋመው የውጭ አገራት ዜጎች የጦር ክፍል ተናግረዋል።
የ X ይዘትን ይለፉትይዘቱን X ይፈቅዳሉ?ማሳሰቢያ: በሌሎች ገጾች ላይ ላሉ ይዘቶች ቢቢሲ ኃላፊነት አይወስድም።ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
