በመላው ዓለም የ1.4 ቢሊዮን ወጣቶች የመስማት ችሎታ አደጋ ላይ ነው፣ ለምን?

በመላው ዓለም የ1.4 ቢሊዮን ወጣቶች የመስማት ችሎታ አደጋ ላይ ነው፣ ለምን?

ስልኮች፣ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች የማድመጫ መሳሪያዎች በስፋት በሁሉም እጅ በሚገኙበት በዚህ ዘመን በተለይ የወጣቶች የመስማት ደኅንነት አደጋ ላይ እንደሆነ አንድ ጥናት አመልክቷል።

በቅርቡ የተደረገው ይህ ጥናት እንደሚለው ከሆነ በመላው ዓለም 1.4 ቢሊዮን ወጣቶች ለከፍተኛ ድምጽ በመጋለጣቻው ምክንያት የመስማት ችሎታቸው እና ጤንነታቸው አደጋ ላይ ወድቋል።

ታዲያ ከዚህ አሳሳቢ ችግር በተለይ ወጣቶች እራሳቸውን እንዴት ሊጠበቁ ይችላሉ? ጤናማ የሚባለው የድምጽ መጠንስ ምን ያህል ነው?