ለፍቅር ሲል የምልክት ቋንቋ የተማረው አፍቃሪ

ለፍቅር ሲል የምልክት ቋንቋ የተማረው አፍቃሪ

ወጣቱ አፍቃሪ የሕይወት አጋሩ ጋር የተገናኙት ከሦስት ዓመት በፊት ነው። ፍቅረኛው መስማትም ሆነ መናገር አትችልም።

እናም ከፍቅረኛው ጋር ለመግባባት የምልክት ቋንቋ ማጥናት ጀመረ። ከሦስት ዓመት በኋላ ቋንቋውን በሚገባ ተምሮ ፍቅራቸውን ከመግለጽ ባለፈ ሌሎች ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ለመርዳት እየሰሩ ነው።

አንዳንድ ጊዜ ጭፈራ ቤት በመሄድ ታዳሚውን ያስደምማሉ። በቀጣይ ደግሞ ጥንዶቹ የውዝዋዜ ችሎታቸውን በአደባባይ የማሳየት እና የምልክት ቋንቋ ነጠላ ዜማ የማውጣት ዕቅድ አላቸው።