ለዓመታት የተደረገው ጦርነት ከቆሻሻ ክምር ምግብ እንዲቃርሙ ያደረጋቸው ሶሪያውያን
ለዓመታት የተደረገው ጦርነት ከቆሻሻ ክምር ምግብ እንዲቃርሙ ያደረጋቸው ሶሪያውያን
ከአስር ዓመታት በላይ የዘለቀው ጦርነት በአንጻራዊነት የተረጋጋች እና ዜጎቿ መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ይነስም ይብዛም ያገኙባት የነበረችውን ሶሪያን አመሰቃቅሏታል።
ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖችን ጨምሮ የተለያዩ አገራት ኃይሎች በተሳተፉበት ጦርነት ሰበብ በበርካታ የሶሪያ ክፍሎች ውስጥ ድህነት ስር ሰዷል።
እነዚህ ታዳጊዎች ደግሞ የእራሳቸውን እና የቤተሰባቸውን ሕይወት ለማቆየት የአሜሪካ ወታደሮች ከሰፈሩበት ካምፕ አቅራቢያ ካለ የቆሻሻ መጣያ ምግብ እየቃረሙ ኑሮን ይገፋሉ።



