ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሰነድ ተከትሎ የተነሱ ውዝግቦች

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሰነድ ተከትሎ የተነሱ ውዝግቦች

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ሁለት ሳምንታትን አስቆጥሯል። የስምምነቱ ዝርዝር ጉዳይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።

በአንጻሩ ከስምምነቱ በኋላ በቀጠናው ብዙ ውዝግቦች ተነስተዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከርም ኢጋድ እና የአረብ ሊግ አባል አገሮቻቸውን ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። ዋና ዋናዎቹ አወዛጋቢ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?