ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ለጨቅላ ሕጻናት የሚሠጠው በዓለም የመጀመሪያው የወባ መከላከያ ክትባት
ለጨቅላ ሕጻናት የሚሠጠው በዓለም የመጀመሪያው የወባ መከላከያ ክትባት
በመላው ዓለም የወባ በሽታ በዓመት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት ይዳርጋል። የዓለም ጤና ድርጅት ማረጋገጫ የሰጠውን ክትባት ጨቅላ ሕጻናትን በመከተብ ካሜሩን የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች።
ካሜሩን በአውሮፓውያኑ 2024 እና 2025 ለ250 ሺህ ሕጻናት ክትባቱን ለመስጠት አቅዳለች። ነገር ግን በአገሪቱ ለክትባት ከሚሰጠው ግምት አንጻር ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል ማሳመን ፈተና ሊሆን ይችላል።