ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ከስታዲየሞች ውጪ ኳታራውያን የዓለም ዋንጫን በተለየ ሁኔታ እየተከታተሉ ነው
ከስታዲየሞች ውጪ ኳታራውያን የዓለም ዋንጫን በተለየ ሁኔታ እየተከታተሉ ነው
ኳታር እያስተናገደችው ያለው የዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ ውድድር የዓለም ሕዝብን ቀልብ ስቧል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተደረጉት ጨዋታዎች ዝግጅቷ የተሳካ መሆኑን አስመስክራለች።
ዜጎቿም እንግዶቻቸውን ከማስተናገድ ባሻገር እነሱም የዓለም ዋንጫ ውድድሮችን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እየታደሙ ነው። በርካቶች በየአካባቢያቸው በተለየ ሁኔታ ተሰባስበው ግጥሚያዎችን በልዩ ዝግጅት ይከታተላሉ።
የቢቢሲ ዘጋቢዎች በዶሃ ዳርቻ በሚገኝ አንድ ቤተሰብ ውስጥ በመገኘት ኳስ የሚከታተሉበትን ሁኔታ ታድመዋል።