ሰዎች ከሌሎቹ የከበሩ ማዕድናት በተለየ ለወርቅ ልዩ ፍቅር ያላቸው ለምንድን ነው?
ሰዎች ከሌሎቹ የከበሩ ማዕድናት በተለየ ለወርቅ ልዩ ፍቅር ያላቸው ለምንድን ነው?
ከጥንታዊው ዘመን ጀምሮ ሰዎች ከፍተኛ ስፍራን ከሚሰጧቸው ማዕድናት መካከል ወርቅ ቀዳሚው መካከል ነው። ከጥንት ነገሥታት ጀምሮ እስከ ተራው ሕዝብ ድረስ ለወቅር ልዩ ቦታ አላቸው።
የዓለም መንግሥታትም የምጣኔ ሃብታቸው የጀርባ አጥንት የሆነውን የገንዘባቸውን ጥንካሬ መተመኛ እና የሃብታቸው ማከማቻ አድርገው ይጠቀሙበታል።
በመላው ዓለም ከጋብቻ ቃል ኪዳን ከሚታሰርባቸው ቀለበቶች አንስቶ እስከ ተለያዩ ጌጣጌጦች ድረስ ከወርቅ ይሰራሉ። ሌሎች ውድ ማዕድናት ቢኖሩም ከታችኛው የኑሮ ደረጃ ካሉ ሰዎች አንስቶ እስከ ባለጸጎች ድረስ የውርቅ ጌጦችን ይጠቀማሉ።
ነገር ግን ወርቅ ከመሬት በታች ካሉ የማዕድን ማውጫ ስፍራዎች ተቆፍሮ ወጥቶ ወደ ተለያየ ጌጥነት ወይም የነጠረ ማዕድን እስኪሆን ድረስ የሚያልፈበት ሂደት ምን ያህል ጉዳትን እንደሚያስከትል ያውቃሉ?



