የልዑል ሃሪ የግል ማስታወሻ መጽሐፍ ውዝግብ ያስነሳባቸው ስድስት ጉዳዮች

የልዑል ሃሪ የግል ማስታወሻ መጽሐፍ ውዝግብ ያስነሳባቸው ስድስት ጉዳዮች

‘ስፔር’ የተሰኘው የልዑል ሃሪ ግለ ታሪክ መጽሐፍ የእንግሊዝኛ ቅጂ ዛሬ ጥር 02/2015 ዓ.ም. ለአንባቢዎች ቀርቧል።

መጽሐፉ ባለፈው ሳምንት በስፓኒሽ ቋንቋ ታትሞ ከተሰራጨ በኋላ በእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰቦች ዘንድ ትልቅ ቅሬታን ፈጥሯል።

ልዑል ሃሪ በግለ ታሪክ መጽሐፉ ላይ በሚስቱ ምክንያት በወንድሙ እንደተደበደበ፣ የኮኬይን ዕፅ ይጠቀም እንደነበር እና አፍጋኒስታን ለወታደራዊ ተልዕኮ በተሰማራበት ጊዜ 25 የታሊባን ተዋጊዎችን መግደሉን ጽፏል።

በመጽሃፉ ዙሪያ የኬንሲንገተን እና የባኪንግሐም ቤተ መንግሥት አስተያየት ለመስጠት ፍላጎት እንደሌላቸው አሳውቀዋል።