ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በርካታ ኢራቃውያን ሴቶች ራሳቸውን በእሳት የሚያቃጥሉት ለምንድን ነው?
በርካታ ኢራቃውያን ሴቶች ራሳቸውን በእሳት የሚያቃጥሉት ለምንድን ነው?
የኢራቅ ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው በ2020 ከነበረው አንጻር በኢራቅ ሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት በ125 በመቶ አሻቅቧል።
በተለይ በኢራቅ ኩርዲስታን ግዛት ውስጥ ያሉ ሴቶች ከሚደርስባቸው ጥቃት ብቸኛ ማምለጫ መንገድ አድርገው የሚቆጥሩት ራሳቸውን በእሳት እያቃጠሉ መግደልን ነው።
የግዛቱ አስተዳደር ይህንን አሰቃቂ ችግር ለመቅረፍ ጥረት ቢያደርግም አሁንም ብዙዎች አደጋ ውስጥ ናቸው።
ቢቢሲ ብዙ ኢራቃውያን ሴቶች ራሳቸውን አቃጥለው ሕክምና ከሚያገኙበት አንዱ እና ትልቁ ሆስፒታል ገብቶ ያለውን ሁኔታ ተመልክቷል።