ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ብልጽግናዎች "ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን አገር ይዘው ሊወድቁ ነው"
ብልጽግናዎች "ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን አገር ይዘው ሊወድቁ ነው"
በኦሮሚያ የነበረውን የወጣቶች 'ቄሮ' ሕዝባዊ ተቃውሞ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም የነበረው ጃዋር 'አልፀፀትም' የተሰኘው መጽሐፉን ታሕሳስ 10 2017 ዓ.ም. በኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል።
ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ መስራቹ ጃዋር በአሜሪካ ከሚገኘው ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ በፓለቲካ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን እንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪውን ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በሰብዓዊ መብት ይዟል።
አቶ ጃዋር ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ብልጽግናዎች "ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን አገር ይዘው ሊወድቁ ነው" ሲል ገዢውን ፓርቲ ወቅሰዋል።
በሚመጣው ምርጫ ይሳተፋሉ? ወደፊትስ ሀገር መምራት ይሻሉ? ተብለው ተጠይቀዋል። እነሆ ፖለቲከኛው ጃዋር መሐመድ ከቢቢሲ ጋር ያደረጉት ቆይታ።