ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ባለፉት አስር ዓመታት ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ለምን ቁጡ ሆኑ?
ባለፉት አስር ዓመታት ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ለምን ቁጡ ሆኑ?
በመላው ዓለም ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ መከፋት፣ ጭንቀት፣ ቁጡነት እየታየባቸው መሆኑን አንድ የሕዝብ አስተያየት መለኪያ ጥናት አመልክቷል።
በዚህም ባለፉት አሥር ዓመታት በየዓመቱ በ150 አገራት ከ120 ሺህ 000 በላይ ሰዎችን ባሳተፈው ጥናት በተሰበሰበው መረጃ መሠረት የሴቶች ብስጭት እየጨመረ መጥቷል።
የጥናቱ ተሳታፊዎች ጥናቱ በተሠራበት ቀን ዋዜማ ምን ዓይነት ስሜቶች እንደተሰሟቸው ተጠይቀው፤ ቁጣ፣ ብስጭት፣ ጭንቀት እና ስጋት የሚሉ የስሜት አማራጮች ሲቀርቡ፣ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ናቸው መበሳጨታቸውን የሚገልጹት። ምክንያቱ ምን ይሆን?