ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩት 72 የቤተሰብ አባላት
በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩት 72 የቤተሰብ አባላት
በእርስዎ ቤተሰብ ውስጥ በአንድ ቤት ምን ያህል ሰው ይኖራል? አስር፣ ሃያ. . .? ብዙ ነው? እሺ ምን ያህል የአንድ ቤተሰብ አባላት በአንድ ስፍራ ላይ ሊኖሩ ይችላሉ?
በሕንዷ ማሃራሽትራ ግዛት የሚገኘው የዶይጆዴ ቤተሰብ ግን አራት ትውልድን በአንድ ጣሪያ ሥር እያኖረ ነው። 72 አባላት አሉት።
ቤተሰቡ ለየዕለት ፍጆታው የሚያውለውን ወተት፣ አትክልት፣ ሩዝና ሌሎች የምግብ ምርቶች በጅምላ ነው የሚሸምተው። ምናልባትም ለንግድ የሚገዙ ሊመስሉ ይችላሉ።
በንግድ ሥራ የሚተዳደረው ሰባ ሁለት አባላት ያሉት ይህ የቤተሰብ በአንድ ላይ መኖራቸው የጥንካሬያቸው ምንጭ ነው ብለው ያምናሉ።
አሁን ያለው የቤተሰቡ አባላት ብቻ ሳይሆን ቀጣዩ የቤተሰባቸው ትውልድም በተመሳሳይ በአንድ ጣሪያ ሥር እንደሚኖር ተስፋ አላቸው።