እስማኤል ሃኒያ ኢራን ውስጥ ከመገደላቸው በፊት የነበሩት የመጨረሻዎቹ ሰዓታት

እስማኤል ሃኒያ ኢራን ውስጥ ከመገደላቸው በፊት የነበሩት የመጨረሻዎቹ ሰዓታት

የሐማስ የፖለቲካ መሪ ኢስማኤል ሃኒያ ኢራን ውስጥ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ተገድለዋል። ኳታር ውስጥ በስደት ይኖሩ የነበሩት ሃኒያ ኢራን የተገኙት በአዲሱ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ሲመተ በዓል ላይ ለመታደም ነበር።

ሃኒያ ቡድናቸው ባለፈው መስከረም ድንገተኛ ጥቃት በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ጋዛ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የተገደሉ ሐማስ ከፍተኛ መሪ ናቸው።

ሐማስ ግድያው በእስራኤል የተፈጸመ ነው ቢልም እስራኤል ግን ማረጋገጫም ሆነ ማስተባባያ አልሰጠችም። ነገር ግን ሐማስ እና ኢራን የሃኒያ ደምን እንበቀላለን ብለው ዝተዋል።