ጆ ባይደን ለፕሬዝዳንትነት መወዳደራቸውን የበለጠ አጠያያቂ ያደረገው የሰሞኑ ስህተታቸው

ጆ ባይደን ለፕሬዝዳንትነት መወዳደራቸውን የበለጠ አጠያያቂ ያደረገው የሰሞኑ ስህተታቸው

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኔቶ ለዩክሬን ስለሚሰጠው ድጋፍ ለጋዜጠኞች በተናገሩበት መድረክ ላይ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪን በስህተት “ፕሬዝዳንት ፑቲን” ብለው መጥራታቸው የበለጠ መነጋገሪያ አድርጓቸዋል።

የ81 ዓመቱ አዛውንት ጆ ባይደን ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ በድጋሚ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት እንዳይወዳደሩ ግፊት እየበረታባቸው ባለበት ወቅት ነው ይህንን ስህተት የፈጸሙት።

ጋዜጠኞች እና የኔቶ አባል አገራት መሪዎች በታደሙበት መድረክ ፕሬዝዳንት ባይደን የፈጸሙትን ስህተት ለመሸፋፈን ጥረት አድርገዋል። ያንን ቅጽበት የሚያሳየው ቪዲዮ በዓለም ዙሪያ በስፋት እየታየ ነው።