አንድ ዓመት በሞላው ጦርነት ለውስብስብ ችግር የተጋለጡት ሱዳናውያን ክርስቲያኖች

አንድ ዓመት በሞላው ጦርነት ለውስብስብ ችግር የተጋለጡት ሱዳናውያን ክርስቲያኖች

ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰው የሱዳን ጦርነት ክርስቲያኖችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። በጦርነቱ መጀመሪያ አካባቢ ክርስቲያኖች በተለየ መልኩ ተጠቅተዋል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ነበር።

አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋል፤ አንዳንዶቹም በከባድ መሣሪያ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከአንድ ዓመት በኋላ ብዙዎቹ ወደ ግብፅ ሲሰደዱ፣ ቀሪዎቹም ተጠልለው ከሚገኙበት ፖርት ሱዳን ለመሰደድ አማራጮችን እየፈለጉ ነው።