በዓለም ዙሪያ የሚሊዮኖችን ሕይወት እየታደገ ነው የሚባልለት የፈጠራ ሰው ማን ነው?

በዓለም ዙሪያ የሚሊዮኖችን ሕይወት እየታደገ ነው የሚባልለት የፈጠራ ሰው ማን ነው?

እአአ በ1958 ነበር ኒልስ ቦህሊን የመኪና ወንበር ቀበቶን እንዲሰራ ኃላፊነት የተሰጠው። የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ኒልስ ሦስት ወራት ብቻ ወሰደበት።

ከዚያ በፊት የነበረው የመቀመጫ ቀበቶ ሰዎች አደጋ በሚደርስባቸው ጊዜ ሆዳቸውን ወይንም አንገታቸውን ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ ነበር። ኒልስ ይህንን ችግር የቀረፈ ሥራ አበርክቷል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኒልስ የፈጠራ ሥራ ሚሊዮኖችን ታድጓል። በአንጻሩ ሥራውን አሜን ብሎ መቀበል የቸገራቸው ሰዎችም ነበሩ።

ይህንን ለማሳመን ኒልስ በመላው ዓለም በየተዘዋወረ በተለያዩ ሙከራዎች አማካይነት የቀበቶውን ጥቅም ያስረዳ ነበር። በ1970ዎቹ ግን የመኪና ወንበር ቀበቶ ማሰር በመላው ዓለም ግዴታ ሆነ።