በሩዋንዳዋ ኪጋሊ ጎዳና ‘ፋስት ፉድ’ የሚሸጡት ኢትዮጵያውያኑ እህትማማቾች

በሩዋንዳዋ ኪጋሊ ጎዳና ‘ፋስት ፉድ’ የሚሸጡት ኢትዮጵያውያኑ እህትማማቾች

ብሌን እና ሰላም ተስፋለም መኖሪያቸውን ሩዋንዳ ካደረጉ ሰነባብተዋል። ብሌን ወደ ሩዋንዳ ያቀናቸው በፍቅር ጓደኛዋ አሌይን ፓትሪክ አማካይነት ነው።

ጓደኛዋ አገሩን እንድታይለት ይወተውታት ነበር። “ወደ ሩዋንዳ ከመጣሁ በኋላ ግን በፍቅሯ ወደቅኩ” ትላለች።

እህቷ ሰላምም “ኪጋሊ ተመችታኛለች” ትላለች። እህትማማቾቹ አሁን መሐል ኪጋሊ ላይ የ‘ፋስት ፉድ’ ሱቅ ከፍተዋል። ኢትዮጵያውያን ኪጋሊን ሊጎበኟት ይገባል ይላሉ።