ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ለአስርታት ሲፈላለጉ የቆዩት አባት እና ልጅ ሳያውቁ በፌስቡክ ላይ ጓደኛሞች ሆነው ተገናኙ
ለአስርታት ሲፈላለጉ የቆዩት አባት እና ልጅ ሳያውቁ በፌስቡክ ላይ ጓደኛሞች ሆነው ተገናኙ
ማኀበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚነሱ አሉታዊ ትችቶች ባሻገር በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ በርካታ ጠቃሚ ጎን አለው። ከእነዚህም መካከል የተጠፋፉ ቤተሰቦችን፣ ዘመዶችን እና ጓደኞችን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ማገናኘቱ ይጠቀሳል።
የታሙና ሙሴሪድዜ ታሪክ ከእነዚህ ውስጥ የሚካተት ከመሆኑ በተጨማሪ ለየት ያለ ነው። በጉዲፈቻ ያደገችው ታሙና እናት እና አባቷን ለማግኘት ባደረገችው ጥረት አባቷ የፌስቡክ ጓደኛዋ ሆነው አግኝታቸዋለች። ይህ እንዴት ሆነ?