የኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ የመላክ ጅምር እና ያለው አገራዊ ፍላጎት
ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት የስንዴ ምርት ወደ ውጭ መላክ መጀመሯን አስታውቃለች። ባለፉት ዓመታት የአገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት 30 በመቶ የሚሆነው ስንዴ ከውጭ ይገባ ነበር።
የመንግሥት መረጃ እንደሚያሳየው ዘንድሮ የአገር ውስጥ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር ከ30 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ወደ ውጭ የመላክ አቅም ተፈጥሯል ተብሏል።
ይሁን እንጂ በጦርነት እና በድርቅ የተጎዱ ዜጎች አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ይፈልጋሉ። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት 10 ሚሊዮን ዜጎች የዕለት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ።









