ዝቅተኛ
ይህንን ዘዴ እንዴት ነው መጠቀም ያለብዎት
ማድረግ ያለብዎ
ይህንን ዘዴ መጠቀም ያለባቸው
- ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
- በጤና ባለሙያ ወይም በቤት ውስጥ የደም ግፊት መጠናቸው የተለካ ሰዎች
ማድረግ የሌለብዎ
ይህንን ዘዴ መጠቀም የሌለባቸው
- ዕድሜያቸው 17 እና ከዚያ በታች የሆኑ
- ነፍሰጡሮች
- የደም ግፊትን የሚያዛቡ መድኃኒቶች የሚወስዱ
- በቅርቡ ቀዶ ሕክምና ያደረጉ ወይም ጉዳት የደረሰነባቸው
- ማዞር፣ ማቅለሽለሽ፣ ወይም ራስ ምታትን የመሳሰሉ ስሜቶች ያላቸው
- ስለደም ግፊታቸው በቅርቡ በጤና ባለሙያዎች የታዩ እና የሕክምና ምክር የተሰጣቸው
- የደም ግፊትዎ የሚያሳስብዎ ከሆነ ሐኪም ያማክሩ።
የደም ግፊታችንን በትክክል ለመለካት የሚጠቅሙ ነጥቦች
በቤትዎ የደም ግፊት ሲለኩ ትክክለኛ ውጤት ለማግኘት መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ።
- መደገፊያ ባለው ወንበር ላይ ቀጥ ብለው ይቀመጡ።
- እግሮችዎን መሬት ላይ አደላድለው ያሳርፉ።
- ክንድዎን ጠረጴዛ ላይ በማሳረፍ ዘና ብለው ይቀመጡ።
- አጭር እጅጌ ያለው ልብስ ይልበሱ።
- የደም ግፊትዎን ሲለኩ ሳያወሩ ዘን ብለው በተለመደው ሁኔታ ይተንፍሱ።
- የውጤቱን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ደግመው ይለኩ።
- የደም ግፊትዎን ጠዋት እና ማታ ይለኩ።













