ግድያና ጠለፋ መገለጫው የሆኑት የሴራሊዮን የወሲብ ንግድ!

በሴራሊዮን በወሲብ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ከድብደባ እስከ ሞት የሚደርስ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል። የአገራቸው ፖሊሶች ሳይቀሩ ጥቃት ያደርሱባቸዋል። አለፍ ሲልም ወደ ሌሎች የምዕራብ አፍሪካ አገራት ተጠልፈው ይወሰዳሉ።

በአንዲት አነስተኛ የሴራሊዮን ከተማ ብቻ ከ1 ሺህ በላይ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶች ይገኛሉ። አንዳንዶቹ ይህንን አጋጣሚ አገሪቱ ከዓመታት በፊት ለ11 ዓመታት ያሳለፈችው የእርስ በእርስ ጦርነት ውጤት ነው ይሉታል።

በዚህ ታሪክ ውስጥ የተካተተችው ኢሳታ በአገሪቱ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶች ከሚደርስባቸው ግፍ መካከል አብዛኛውን አልፋበታለች።