የላዳ ታክሲ ሹፌሩ በጎ ተግባር
ሰለሞን ተዘራ ይባላል። ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ሲሆን የላዳ ታክሲ ሹፌር ነው። ከሥራው ጎን ለጎን ጎዳና ላይ የሚያገኛቸው የአዕምሮ ሕሙማንን እና አረጋዊያንን በማጠብ እና ልብስ ለምኖ በመስጠት የበጎ ፈቃድ ሥራ ይሰራል። ከ2 ዓመት በፊት ይህንን ሥራ የጀመረው ሰለሞን እስካሁን 750 ሰዎችን መርዳቱን ይናገራል። "ሥራ ሰርቼ ከማገኘው ገቢ በላይ አረጋዊያንን ገላ አጥቤ የማገኘው የሞራል እርካታ ይበልጥብኛል" ይላል።