መጽሐፉን በአማርኛ ያዘጋጀሁት ታላሚ አንባቢዎቼ አማርኛ አንባቢዎች ስለሆኑ ነው- አፈንዲ ሙተቂ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, መጽሐፉን በአማርኛ ያዘጋጀሁት ታላሚ አንባቢዎቼ አማርኛ አንባቢዎች ስለሆኑ ነው፡ አፈንዲ ሙተቂ

አፈንዲ ሙተቂ በኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን መጽሃፍ ጽፏል። መጽሐፉን የጻፍኩት ለአማርኛ አንባቢዎች የኦሮሞን ታሪክ ለመንገር አስቤ ነው ብሏል። ከአማርኛ በተጨማሪ በእንግሊዝኛ እንደሚተረጎምም ገልጿል። ይህኛው የመጀመሪያ ክፍል ሲሆን ክፍል ሁለትን ለማዘጋጀት ማቀዱንም ተናግሯል። አፈንድዲ ይህንን መጽሐፍ ለማዘጋጀት በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ታሪኩን ለማዳበር ታሪክ አዋቂዎችን እና ሽማግሌዎችን እንዳነጋገረ ገልጿል።