ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ኮሮናቫይረስ፡ በኮሮናቫይረስ ዳግም ከመያዝ እንድን ይሆን?
በኮሮናቫይረስ ተይዘን ካገገምን በኋላ በሌላ አጋጣሚ ድጋሚ በቫይረሱ ልንያዝ እንችል ይሆን? ኮሮናቫይረስ አዲስ ወረርሽኝ በመሆኑ በቫይረሱ ዙሪያ ለሚነሱ ሳይንሳዊ ጥያቄዎች ተመራማሪዎች በቂ ምላሽ መስጠት አልቻሉም። አንደኛውና ወሳኙ ጥያቄ በበሽታው ተይዘን ካገገምን በኋላ ድጋሚ ላለመያዛችን ዋስትናችን ምንድን ነው? የሚለው ነው። በዚህ ጉዳይ ሳይንቲስቶች ይህንን ይላሉ።