ኮሮናቫይረስ እያስከተለ ካለው ቀውስ ባሻገር ተስፋ ይዞ ይመጣ ይሆን?
ቀደም ባሉት ዘመናት በመላው ዓለም የተለያዩ ወረርሽኞች ተከስተው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ቀጥፈዋል። በምጣኔ ሃብት ረገድም ከባድ የሚባል አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደረቸው ይነገራል።
በአንጻሩ ደግሞ እነዚህ ወረርሽኞች ከመከሰታቸው በፊት ያልነበሩ አዳዲስ ነገሮችን በማምጣትም ዓለም እንደገና እንድትሰራ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ከዚህ አኳያ ኮሮናቫይረስ እያስከተለ ካለው ከቀውስ ባሻገር ምን ተስፋ ይዞ ይመጣ ይሆን?