የህመም ስሜት ባይሰማንም ቫይረሱ እንዳለብን እንዴት ማወቅ እንችላለን?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የህመም ስሜት ሳይሰማን ነገር ግን ቫይረሱ እንዳለብን እንዴት ማወቅ እንችላለን?

በአሁኑ የጉዞ ታሪክም ሆነ የውጭ ጉዞ የሌላቸው ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተጠቅተው እየተገኙ ነው። በዚህ ምክንያትም ብዙ ሰዎች ተጋላጭነታቸው ጨምሯል። በመሆኑም የህመም ስሜት ሳይሰማን ነገር ግን ቫይረሱ እንዳለብን እንዴት ማወቅ እንችላለን? የጤና ሙያተኞች እንደሚያስረዱት አንድ ሰው በኮሮናቫይረስ ከተያዘ በኋላ ከሁለት እስከ 14ኛው ቀን ድረስ ምልክት ላያሳይ ይችላል።

አንዳንዴም እስከ 21ኛው ቀን ድረስ ቫይረሱ ያለበት ሰው ምልክት ላያሳይ ይችላል። በእነዚህ ጊዜያት ታዲያ ግለሰቡ ለሌሎች ሰዎች ቫይሱን ያስተላልፋል።