ኮሮናቫይረስ ድጋሚ ያገረሽ ይሆን?

በታኅሳስ ወር አጋማሽ በቻይና ዉሃን የተከሰተው ኮሮናቫይረስ መላው ዓለምን አጥለቅልቋል። በሽታው የተከሰተባት ቻይና በአንጻሩ ወረርሽኙን ገትታዋለች። በሌሎች የዓለማችን ክፍሎች ግን ቫይረሱ አሁንም ፈተና እየሆነ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ቫይረሱ ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። ለመሆኑ አንድ ወረርሽኝ እንዴት ድጋሜ ሊያገረሽ ይችላል? ኮሮናቫይረስስ የማገርሸት እድሉ ምን ይመስላል?