የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን?

የአውሮፕላን በረራ የሚጀመረው መቼ ይሆን?

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አገራት ከወሰዷቸው እርምጃዎች መካከል አንዱ በሆነው በአየር ትራንስፖርት እገዳ ምክንያት ዘርፉ ክፉኛ ተዳክሟል። በየዕለቱ በዓለም ዙሪያ ይደገሩ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ በረራዎች በመሰረዛቸው የንግድ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በአብዘኛው ተቋርጧል።

በዚህ ዓመት በዓለም ደረጃ የአየር ትራንስፖርቱ ዘርፍ 84 ቢሊዮን ዶላር ይከስራል ተብሎ ተገምቷል።

በዚህም ሳቢያ አየር መንገዶች እከሰሩ ሠራተኞቻቸውን ከመቀነስ በተጨማሪ የተዘጉም አሉ። ለወራት በወረርሽኙ ምክንያት የተስተጓጎለው የአየር ትራነስፖርት መቼ ይጀምራል? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

ባለሙያዎች በረራዎችን መልሶ ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ያሏቸውን ጉዳዮች ያነሱበትን ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ።