ባህላዊ የሳፋየር ማዕድን ፍለጋ በትግራይ

ከአክሱም 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የሳፋየር ማእድን ፍለጋ ቀን ከሌት ይለፋሉ። የቀናው አንድ ግራም እስከ 50 ሺህ ብር ድረስ ይሸጣል። ያልቀናው ላቡን አንጠፍጥፎ ባዶ እጁን እያጨበጨበ ይመለሳል።