የጥምቀት በዓል አከባበር በጎንደር

ጥምቀት በጎንደር ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች በተለየ ደመቅ ብሎ ይከበራል፡፡ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ጎብኚዎችም ጥምቀትን በአፄ ፋሲል መዋኛ ያሳልፋሉ፡፡ ለበዓሉ ወደ ጎንደር ጎራ የሚሉ ቱሪስቶች በከተማዋም ሆነ በአቅራቢዋ የሚገኙ ቦታዎችን ጎብኝተው ይመለሳሉ፡፡